Total Pageviews

Thursday, January 3, 2013

“አይን እያላቸው የማያዩ ፤ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ”

በዳዊት መላኩ ሞገስ (ከጀርመን)


ወያኔ/ኢህአዴግ የተፈጥሮ ባህሪው በሰዎች መካከል ጥርጣሬና ጥላቻን በዝራት በመሆኑ በማናኛውም ቦታ ረጅም እጁን በማስገባት መፈትተፍ የዘወትር ተግባሩ ሁኖ ቆይቷል፡፡ላለፉት 11 ወራት
የእስልምና እምነት ተከታዮችን የሀባሽ አስተምሮን በግድ ለመጫን በፈጠረው ጣልቃ-ገብነት በሺ የሚቆጠሩትን ለስደት ፤በርካቶችን ለእስራት እና ለሞት ሲዳርግ የቆየውና አሁንም ድረስ መቋጫ ያልተገኘለት ውዝግብ ውስጥ የገባው ወያኔ/ኢህአዴግ አሁን ደግሞ የጥፍት ቀስቱን በክርስትና እምነት ተከታዮች እና በቤተ-ክርስቲያን ላይ አነጣጥሯል፡፡
ወያኔ/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣ ማግስት ጀምሮ ለአገዛዙ  አይመቹኝም ብሎ የተጠራጠራቸውን ሁሉ በማስወገድ ህዝባዊ ተቋማትን፣የእምነት ተቋማትን፣ የትምህርት ተቋማትን እንዲሁም በሀገሪቱ ያሉ መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በወያኔ ካድሮዎች እንዲመሩ በማድረግ የፖለቲካ አቋማቸው እንጂ የትምህርት ዝግጂታቸውና የስራ ልምዳቸው  ፈጽሞ  የማይምጥናቸው አቅመ-ደካሞችን በማስቀመጥ የሀገሪቱን እድገት ቁልቁል እንደካሮት እንዲሆን አድርጎታል፡፡የዚህ ችግር የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ የሆነችው ደግሞ ቅድስት ቤተክርስቲያንና   በውስጧ ያሉት አማኞች ናቸው፡፡በዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን ወደ ሶስት እንድትከፈል በርካታ አባቶችም ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እና ክርስቲያኖችም እርስ በርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩ አድረጎ ቆይቷል፡፡የአቡነ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ የቤተክርስቲያንን አንድነት ለማስመለስ በተለያዩ ሰላም ወዳድ እና የቤተክርስቲያን ተቆርቃሪ ወገኖች ብዙ ሲደከም ቢቆይም ወያኔ/ኢህአዴግ ይቅርታና እርቅ ለባህሪያቸው ስለማይስማማ እና የሰላምን ዋጋ የሚያዩበት አይናቸው ስለተሰወረ የእርቀ-ሰላሙን ገመድ ለመበጠስ ጫፍ ደርሰዋል፡፡በክልሎችና በእምነት ተቋማት በህጋዊነት ሽፋን  ስም ጣልቃ ለመግባት ያቋቋመው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አቡነ ጳውሎስ ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ በጋራና በተናጠል የቤተክርስቲያኒቱን አባቶች በማነጋገር ለስውር አላማው መጠቀሚያ ሊያደርጋቸው ሲነቀሳቀስ ቆይቷል፡፡የሚኒስትር መ/ቤቱ በዚህ ብቻ ሳይወሰን  አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸውንናበእስራኤል ነዋሪ ሆኑትን አባት  ጳጳስ ለማድረግ ልኡካን በመላክ  አላማየን ሊስፈጽሙልኝ  ይችላሉ በማለት  ያመነባቸውን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ  ለመጫን ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡  ለቤተክርስቲያን አንድነት ሲደክሙ ከቆዩት አባቶች መካከልም ሊቀካህናት ሀይለስላሴ አለማሁን መንግስት ለመገልበጥ እንጂ ለማስታረቅ አልመጡም በማለት በሚታወቅበት ጥላሸት መቀባት ተግባሩ ጥላሸት ቀብቶ ወደመጡበት አሜሪካ አስሮ መልሷቸዋል፡፡
ወያኔ/ኢህአዴግ በየቤተክርስቲያኑ የሰገሰጋቸው ካድሬዎችም ከቤተክርስቲያንና ከምእምናኑ ጥቅም ይልቅ ቅደሚያ ለወከላቸው መንግስት ስለሚሰጡ ሰበብ በመፈለግ እርቀ-ስላሙ የሚቋረጥበትን መንገድ እየጠረጉ ገይኛሉ፡፡ለዚህም ተግባራቸው ማሳያ የሚሆነው አሰታራቂ ኮሚቴው ገለልነኛ አደለም፤ይቅርታ ካልጠየቀ አንደራደርም በማለት የማደናገሪያ መግለጫዎችን በመስጠት ለመለያቱ በር እየከፈቱ ይገኛሉ፡፡ በተቃራኒው ሊቆሙለት የሚገባውን የቤተክርስቲያንን አንድነት የማስጠበቅ አና የእምነት ነጻነትን የማስከበር ጉዳይ ወደጎን በማሽቀንጠር ለግል ጥቅማቸውና ስልጣናቸውን ለማቆየት ከአጥፊወች ጎን ተሰልፈዋል፡፡
ከወያኔ ያለፉት ልምዶችና ከተፈጥሮ ባህሪው ለመረዳት የሚቻለው በሀይል እንጂ በድርድር፣በእርቅ፣ስጥቶ የመቀበል መርህ የመሳሰሉት ተግባሮች ስለማይገቡት ከሚወደው ስልጣን ኮርቻ እስካልወረደ ድረስ የፈጠራቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ከኢትዮጵያውያን ጫናቃ ላይ በቀላሉ ሊወርዱ አይችሉም፡፡ወያኔ/ኢህአዴግ እርቀ-ሰላሙን ከልብ ይቀበላል ማለት “ከእባብ እንቁላል የዶሮ ጫጩት እንደመጠበቅ ይቆጠራል፡፡”ይህን ለመገመት የግድ ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡ ወያኔ/እህአዴግ በርካታ ጊዜያት ብሄራዊ እርቅ እንደወርድ በተለያዩ ሀይሎች ለበርካታ ጊዜ ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡ነገር ግን የተፈትሮ ባህሪያቸው የህን ለማስተናገድ አይስማማውም፤አይናቸውም ሰላም ሰፍኖ  ለመየት ፤ጆሮዋቸውም የሰላም ድምጽ ለመሽማት አይፈልግም፡፡መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ኢትዮጵያውያን  በጋራ በሀይል የተነፈግናቸውን መብቶች ሁሉ ማስከበር፡፡
እግዚያብሄር ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!