Total Pageviews

Wednesday, November 28, 2012

በጉዲፈቻ ወደ ዴንማርክ የመጣች ህጻን ለከፍተኛ የስነ አዕምሮ ችግር መዳረጎን ከዴንማርክ የደረሰን ዘገባ አመለከተ

ኢሳት ዜና:-የዛሬአራት አመት ከወላጅ እናቷና አባቷ ተረክበው ህጻኗን ከወንድሟ ጋር የወሰዳት የዴንማር ሰዎች ህጻኗ ለቤተሰቦቿ ያላትን ናፍቆት በየአጋጣሚው በመግለጽ እናቷ ጋር እየዲወስዷት በመጠየቅና ያልተለመደ በሀሪእያሳየች ደስታ በማጣቷ ለህጻናት ማሳደጊያ እንደሰጧት የኢሳት ምንጮች ከዴንማርክ ገልጣለች::
ከዴንማርክ የደረሰን ይሀው መረጃ እንደሚያመለክተው የህጻኗ ማእሾ ታሪክ በዴንማርክ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ቤተሰቦቿን ያነጋገረና የህጻኗን ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ጽኑ ፍላጎት ያሳየ ዶክመንተሪ ፊልም ተሰርቶ በቴሌቭዥን መሰራጨቱን ለምንጮቻችን ገልጻለች::
በህጻኗና በወላጆቿ ፍላጎት ወደ ሃገር ቤት መመለስ በሚለውና የለም መመለስ የለባትም በሚለው ላይ የዴንማርክ ህዝብ ድምጽ እንዲሰጥ ተደርጎ 67 ከመቶው ህጻኗ ወደ ሀገሯ ትመለስ በማለት ድምጽ መስጠቱን ምንጮች አረጋጠዋል::
17 ከመቶየአፍ መፍቺያ ቋንቋዋን ረስታለችና መመለስ የለባትም ሲሉ 20 ከመቶዎቹ ድምጽ ከመስጠት መቋጠባቸውንም ለማወቅተችሏል::
በህጻኗህይወት ታሪክ ዙሪያ ተሰርቷ በተሰራጨው ዶክመንተሪ ፊልም የህጻኗ ወላጆች ልጃቸው እንድትመልስ እያለቀሱ ሲለምኑ የሚታይ ሲሆን  የህጻኗ ጤናን ያሳባ የስነ አእምሮ ችግርም ህጻኗ እንዳጋጠማትም ፊልሙን የተመለከተው ምንጫችን ከዴንማር በስልክ ገልጻለች::
የደን ማርጥ ዜጋ አንድ ህፃን ወደ ሃገሩ ሲያመጣ ከ450 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እንደሚከፍል የምንጮቻችን ዘገባ ያመለክታል::

No comments:

Post a Comment