ኢሳት ዜና:-አቶ በረከት ስምዖን በሚስተር ዡ ሾሼን የተመራ የጋዜጠኞች ልዑካን ቡድንን አነጋግረዋል። የመላው ቻይና ጋዜጠኞች ማህበር ዋና ፀሐፊ ሚስተር ዝሁ ሾቼን የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን አቅም ለመደገፍና የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ቻይና የረጅም ዓመታት የዳበረ ልምድና ተሞክሮ ያላት አገር መሆኑን በመጥቀስ ኢትዮጵያ ከቻይና ልምድ ለመቅሰም እንደምትፈልግ ገልጸዋል።ቻይና በአለም ላይ ካሉ በፕሬስ አፈና ከሚታወቁ አገሮች ተርታ ትመደባለች። የኢንተርኔት ስርጭቶችን በማፈን ድረገጾችን በመዝጋት የሚታወቀው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ስልጠና ለመስጠት መዘጋጀቷ ገዢው ፓርቲ በፕሬስ አፈናው ለመቀጠል መቁረጡን የሚያሳይ ነው በማለት የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።
No comments:
Post a Comment